Skip to main content

ዓለም ዓቀፍ፡ በግጭት ውስጥ ከፍተኛ አደጋ ላይ ያሉ አዛውንቶች

ሁሉም መንግስታት እና የተባበሩት መንግስታት ሰዎች ላይ ያላግባብ የሚደርስ ችግር ለማስቆም፣ ጥበቃን ለማረጋገጥ እና እርዳታ ለመስጠት የበለጠ መስራት አለባቸው፡፡

(ኒውዮርክ) – ሂዩማን ራይትስ ዎች ዛሬ ባወጣው ዘገባ መሠረት አረጋውያን ብዙውን ጊዜ በትጥቅ ግጭቶች ወቅት ለመብት ረገጣዎች እንደሚጋለጡ ገልጿል። ሁሉም በትጥቅ ትግል ውስጥ የሚሳተፉ አካላት በአረጋውያን ላይ የሚደርሰውን በደል ማቆም እና የተቸገሩ አዛውንቶች ሰብአዊ እርዳታ ማግኘት እንዲችሉ ማመቻቸት አለባቸው ይላል። የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤትም በትጥቅ ግጭቶች ውስጥ ላሉ አረጋውያን ሲቪሎችን የተጠናከረ ጥበቃ መኖር አስፈላጊነት ተገንዝቦ ይህንን ማረጋገጥ አለበት ሲል ያትታል።

ባለ 48 ገፁ የሂማን ራይትስ ዎች ዘገባ እንደሚያሳየው ከሆነ “የትጥቅ ግጭት በሚካሄድበት ስፍራ የሚኖሩ አዛውንቶች በደል ሳይፈጸምበት የሚተርፍ ሰው የለም”፡፡  እ.ኤ.አ ከ 2013 እስከ 2021 በቡርኪና ፋሶመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ኢትዮጵያ፣ እስራኤል እና በተያዙት የፍልስጤም ግዛቶች፣ ማሊ፣ ሞዛምቢክ፣ ናጎርኖ፡ካራባክኒጀር፣ ደቡብ ሱዳንሶሪያ እና ዩክሬን አረጋውያን ላይ ይደርስ የነበረውን የመብት ጥሰት ማሳያ ናቸው ይላል። ዘገባው በተጨማሪም በካሜሩን ውስጥ በሁለት እንግሊዘኛ ተናጋሪ ክልሎች የተከሰተውን ከባድ የረዥም ጊዜ ብጥብጥ፣ የሚያንማር የጸጥታ ሃይል በራኪን ግዛት ውስጥ በእድሜ የገፉ የሮሂንጊያ ጎሳ አባላት ላይ የፈፀመውን ግፍ እና በሶሪያ ግጭት ሳቢያ በሊባኖስ ስለሚኖሩ አረጋውያን ስደተኞች ተሞክሮ ይጠቅሳል።

በሂዩማን ራይትስ ዎች የአረጋውያን መብት ከፍተኛ ተመራማሪ ብሪጅት ስሊፕ “ሽማግሌዎች በግጭቶች ወቅት ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር እና ጠለፋን ጨምሮ ከባድ በደል ይደርስባቸዋል። በመሆኑም መንግስት እና የተባበሩት መንግስታት የአረጋውያንን ልዩ አደጋዎች እና የእርዳታ ፍላጎቶች ተገንዝበው እነሱን ለመጠበቅ እርምጃ እንዲወስዱ አስቸኳይ ፍላጎት አለ’’ ይላሉ።

የመንግስት ሃይሎች እና መንግስታዊ ያልሆኑ ታጣቂዎች በአለም ላይ በተከሰቱ ግጭቶች ሁሉ በእድሜ የገፉ ንፁሀን ዜጎች ላይ ጥቃት እና ከባድ በደል ፈጽመዋል፡፡ እነዚህም ህገወጥ ግድያ፣ ፍርድ የሌለው ግድያ፣ የዘፈቀደ እስራት፣ ማሰቃየት እና ሌሎች እንግልቶችን፣ አስገድዶ መድፈርን፣ መጥለፍ፣ አፍኖ መሰወርን እንዲሁም ቤታቸው እና ንብረታቸው ማውደምን ያጠቃልላሉ። በእድሜ የገፉ ሰላማዊ ሰዎች ስፋት ባለው አከባቢ በአነስተኛና በከባድ መሳሪያዎች፣ በፈንጂዎች፣ በኬሚካል እና በሌሎች የተከለከሉ መሳሪያዎች ተገድለዋል፣ ቆስለዋል፥፥ አረጋውያን ብዙውን ጊዜ ጥቃትን ለመሸሽ በማይችሉበት ጊዜ ወይም በቦታቸው መቆየት ሲመርጡ ለአደጋ ይጋለጣሉ።

በቡርኪናፋሶ እና ማሊ የታጠቁ እስላማዊ ቡድኖች፣ የመንግስት ሃይሎች እና የጎሳ ታጣቂዎች ታዋቂ የሀገር ሽማግሌዎችን ጨምሮ በርካታ አዛውንቶችን ገድለዋል። እ.ኤ.አ ጃንዋሪ 27፣ 2022 የማሊ ጦር በሰማኒያዎች እድሜ የሚገኙ እና 12 ሌሎች ሰዎች በቶና፣ ማሊ መንደር ላይ የሞት ቅጣት ተወስዶባቸዋል።

በደቡብ ሱዳን ከአስገድዶ መድፈር የተረፈች በ50ዎቹ እድሜ መጨረሻ የምትገኝ ሴት መንግስት በፌብሪዋሪ 2019 በአማጺ ሃይሎች ላይ ባደረገው ዘመቻ አንድ ወታደር የተዘረፈ ንብረት እንድትይዝ እንዳደረጋት፣ በሽጉጥ እንደ ደበደባት እና ደጋግሞ እንደደፈራት ተናግራለች።

እ.ኤ.አ በዲሰምበር 2016 እና ኤፕሪል 2017 መካከል የሶሪያ መንግስት የጦር አውሮፕላኖች ሳሪን የተባለ ኬሚካልን ጨምሮ ነርቭን የሚነካ ኬሚካል ተጠቅሞ አራት ግዜ ጥቃቶችን ፈጽመዋል። በኬሚካሉ ለጥቃት ተጋልጠው ከሞቱት መካከል በዕድሜ የገፉ ሰዎች ይገኙበታል።

በጦርነቱ ወቅት፣ በብዙ አጋጣሚዎች የመንቀሳቀስ ውስንነት ያላቸው ወይም የተለያዩ አካል ጉዳተኛ የሆኑ አዛውንቶች ጦርነቱ ሲቃረብ ለመሸሽ ከሌሎች ድጋፍ አያገኙም እና ወደ ኋላ መቅረት የሚገደዱበት ሁኔታ ይታያል። እ.ኤ.አ በ2017፣ ከሚያንማር በግዳጅ የተባረሩት ሮሂንጊያዎች የጸጥታ ሃይሎችን መሸሽ የማይችሉ አረጋውያንን ወደ ተቃጠሉ ቤቶች እየገፉ እንዳስገቡ ተገልጿል። “የባለቤቴን አጎት ወደ እሳቱ ሲገፋት አይቻለሁ። ወደ ሚቃጠለው ቤት ሲገፉት አይቻለሁ” ስትል አንዲት ሴት ተናግራለች። “ደካማ ነው፣ ምናልባት 80 ዓመት ዕድሜ። ሁሉም ሰው እንዲሄድላቸው ፈልገው መሄድ ያልቻሉትን ግን ወደ እሳት ውስጥ አስገብተዋቸዋል’’ ስትል ተናግራለች።  

ሌሎች አረጋውያን ንብረታቸውን ለመጠበቅ ሲሉ ከቤታቸው ላለመሸሽ መርጠዋል። እ.ኤ.አ በ2020 በአዘርባጃን ውስጥ በናጎርኖ፡ካራባክ ላይ በተፈጠረው ግጭት አብዛኞቹ ወጣት ሲቪሎች ተሰደዋል። ከጥቂቶች በስተቀር የቀሩት በዕድሜ የገፉ ሰዎች ነበሩ። በዕድሜ የገፉ፣ ለኣብነት በ70ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሴት እና ባለቤታቸው አሬጋ እና ኤድዋርድ ንብረታቸውን ለመጠበቅ በመንደራቸው ቆይተዋል። በጥቅምት ወር የአዘርባጃን ወታደሮች ጥንዶቹን እቤት ውስጥ አገኟቸው እና ያዙዋቸው፣ መጀመሪያ ላይ ያለ ምግብ እና ውሃ ባዶ በቀሩ ቤቶች ውስጥ ኣሰሩዋቸው፣ ከዚያም አዘርባጃን ዋና ከተማ ባኩ ወደሚገኝ እስር ቤት ወሰዷቸው። አሬጋ ለደም ግፊትዋ መድሐኒት እንዳታገኝ በባለሥልጣናቱ ተከልክላለች። ኤድዋርድም በእስር ላይ እያለ ሂወቱ አልፏል። ከሞተ በኋላ ብዙም ሳይቆይ አሬጋ የባለቤቷን ፊት ስትመለከት ጥቁር እና ሰማያዊ ሆኖ ኣይቸዋለሁ ስትል ገልጻለች። 

የተፈናቀሉ አረጋውያን ከእንግልት በተጨማሪ ሰብአዊ እርዳታ እንዳያገኙ እንቅፋት ሲገጥማቸው ይታያል። በደቡብ ሱዳን እ.ኤ.አ. በ 2017 አንድ የ70 ዓመት አይነስውር የነበረ ሰው በተፈናቀሉበት ደሴት ላይ እርዳታ ማግኘት እንደማይቻል ተናግሯቸዋል። “አንዳንድ ድርጅቶች አረጋውያንን መዝግበዋል ነገር ግን ወደዚህ ደሴት ስላልመጡ እኔ ልመዘገብ ኣልቻልኩም” ብሏል። "በደሴቲቱ ላይ ምንም የጤና ክሊኒክ የለም. የሕክምና እርዳታ ለማግኘት ወደ ሌላ ደሴት ወይም ወደ መሃል አገር መሄድ ይኖርብኛል‘’ ብሏል።

የአለም አቀፍ የሰብአዊነት ህግ፣ የጦርነት ህጎች፣ በትጥቅ ግጭቶች ወቅት በዕድሜ የገፉ ሲቪሎች ጥበቃን የማግኘት መብት እውቅና ይሰጣል። በእድሜ የገፉ ሰላማዊ ዜጎችን እና ሌሎችም ከወታደራዊ ዒላማዎች አከባቢ በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲርቁ እና ለታሰሩ ሰላማዊ ዜጎችም እድሜያቸውን ያገናዘበ ተስማሚ ማረፊያ ማዘጋጀትን ይጠይቃል። አረጋውያንም በማንኛውም ጊዜ በሚመለከተው ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ህግ መጠበቅ ይኖርባቸዋል። 

"የተባበሩት መንግስታት ኤጀንሲዎች፣ የሰላም ማስከበር ተልእኮዎች እና የሰብአዊ እርዳታ ስራ ላይ የተሰማሩ ተዋናዮች በሚያደርጉት የእርዳታ ተግባራት የአረጋውያንን ጥበቃ እና ልዩ ፍላጎቶቻቸውን ያካተተ መሆኑን ማረጋገጥ አለባቸው" ስትል ስሊፕ ተናግራለች። "አረጋውያን ያላቸው ልዩ የጥበቃ ፍላጎት በመገንዘብ፣ የትጥቅ ግጭቶች ሰለባ እንዳይሆኑ መስራት ይገባል’’ ይላል።

Your tax deductible gift can help stop human rights violations and save lives around the world.