Skip to main content

ሳውዲ አረቢያ: የስደተኞች ጅምላ ግድያ በየመን ድንበር

በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰው ስልታዊ በደል በሰብዓዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል ተደርጎ ይቆጠራል።

Read a text description of this video

Text on Screen:

WARNING

This video contains violent images and descriptions including people being shot at, and dead bodies. Viewer discretion advised.

Actor’s Voices have been used to protect the identity of the people Human Rights Watch interviewed for the film.

Audio recording, Actors’ Voice:

Even when I remember, I cry. I saw a guy calling for help, he lost both his legs. He was screaming and saying, “are you leaving me here? Please don’t leave me.” We couldn’t help him because we were running for our lives.

Voiceover:

Ethiopian migrants and asylum seekers have been tortured, injured or killed by Saudi Arabian border guards at the Yemen-Saudi border. At least hundreds have been killed trying to make this crossing between March 2022 and June 2023.

Audio recording, Actors’ Voice:

When Saudi border guards see a group, they fire continuously, when they kill everyone, they go down to collect all those who didn't die. This is what happened to me. I survived, and they came to meet me and showed me the dead. Then they took us to a detention center and beat us all there.

Voiceover:

Human Rights Watch’s extensive investigation includes firsthand accounts from 42 people, and the verification and geolocation of over a hundred videos and photos and the analysis of hundreds of square kilometers of satellite imagery. We found evidence that Saudi border guards have used explosive weapons and shot people at close range.  In what appears to be a policy targeting migrants and asylum seekers, including women and children, at the border. Human Rights Watch believes this may amount to crimes against humanity. Saudi Arabia’s border forces should stop intentionally using lethal force, to kill Ethiopian migrants and asylum seekers with explosive weapons.

Audio recording, Actors’ Voice:

It was during the night. We were traveling towards the Saudi border. Then we saw Saudi border guards. They told us to stop. While they walked towards us, they opened fire and fired bullets at us. One bullet hit a rock and hit my leg. My leg is broken around my knee.

Voiceover:

While many migrate for economic reasons, including drought, a number of Ethiopians have fled because of serious human rights abuses by their government, including during the recent, brutal armed conflict in northern Ethiopia.

Audio recording, Actors’ Voice:

When the firing stopped the Saudi border guards took us. In my group there were seven people, five men and two girls. The border guards made us remove our clothes and told us to rape the girls. The girls were 15 years old. One of the men refused. The border guards killed him on the spot. I participated in the rape, yes. To survive I did it. The girls survived because they didn’t refuse. This happened at the same spot where the killings took place.

Voiceover:

This dangerous migration route, often referred to as the 'Eastern route', spans from the horn of Africa, across the Gulf of Aden,

through Yemen and into Saudi Arabia. Migrants and asylum seekers

crossing into Saudi Arabia usually do so in the mountainous border area, aided by a network of smugglers and traffickers and facilitated by the Houthi forces

who control northern Yemen.

Audio recording, Actors’ Voice:

We walked in the mountains for about five days. We walked in groups, minimum 300 people, and most of the group was female. Then there was firing from the border guards, and they were firing big rocket launchers at us. It was like a bomb.  Of the 300 people, 150 died.

Voiceover:

Smugglers operating in Yemen take people to two informal camps before attempting to cross the border. Al Thabit camp is located northwest of the border, and Al Raqw camp has only a river separating it from Saudi Arabia. Both camps act as holding areas with thousands of people preparing to cross the border.  Many interviewees said Houthi forces controlled the entry and exit into the camps and would often extort bribes from the

migrants or transfer them to detention centers. Migrants and asylum seekers often saw Saudi border guards patrolling the crossing points in large vehicles with what witnesses described as large objects mounted on the back of their vehicles, believed to be weapons. Human Rights Watch interviewed survivors who say they lost one or more limbs due to the use of explosive weapons or shootings at the border.

Audio recording, Actors’ Voice:

The Saudi border guards were firing big things like mortars at us. They fired from the back of a truck. We lost 130 people that day, the majority were women and children.

Voiceover:

Although the number of deaths has not been confirmed, Human Rights Watch has identified at least eight burial sites near Al Raqw camp and has counted at least 287 graves on satellite images as of June 2023.  Many have described bodies being buried in remote areas or left unburied along the route. They describe a pattern of large scale violence and cross-border killings. This video was sent to and verified by Human Rights Watch. The video shows the bodies of at least two migrants hidden under bushes just north of the trail from Al Thabit camp in Saudi Arabia. A likely Saudi border guard post is visible approximately 1.3 kilometers away from where the bodies were found. 

Voiceover:

Humanitarian assistance and safe passage should be provided to migrants and asylum seekers trying to cross the border from Yemen to Saudi Arabia, and those responsible for what may amount to crimes against humanity should be held accountable.

  • የሳውዲ ድንበር ጠባቂዎች ከመጋቢት 2022 እስከ ሰኔ 2023 ባለው ጊዜ ውስጥ የየመን-ሳውዲን ድንበር ለመሻገር በሞከሩት በትንሹ በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችንና ጥገኝነት ፈላጊ ኢትዮጵያውያንን ገድለዋል።
  • የሳውዲ ባለሥልጣናትም በአንድ በኩል የራሳቸውን ገፅታ ለመገንባት በስፖርታዊ ውድድር ላይ በቢሊዮኖች ወጪ ሲያደርጉ በሌላ መልኩ ደግሞ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሴቶችና ሕፃናትን ከቀረው ዓለም እይታ በተሰወረ መንገድ ይገድላሉ።
  • ሳውዲ አረቢያ በስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ላይ የምትከተለውን ገዳይ ፖሊሲ ጊዜ ሳትሰጥ በአስቸኳይ መሻር አለባት። ጉዳዩ የሚመለከታቸው አገሮች በበኩላቸው ተጠያቂነት እንዲኖር ግፊት ማድረግ ያለባቸው ሲሆን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም በጉዳዩ ዙሪያ ምርመራ ማካሄድ አለበት ።

(ለንደን) ሂዩማን ራይትስ ዎች ዛሬ ያወጣው ሪፖርት እንደሚገልፀው፣ የሳውዲ ድንበር ጠባቂዎች ከመጋቢት 2022 እስከ ሰኔ 2023 ባለው ጊዜ ውስጥ የየመን–ሳዑዲን ድንበር ለመሻገር የሞከሩትን በትንሹ በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችንና ጥገኝነት ፈላጊ ኢትዮጵያውያንን ገድለዋል። ስደተኞችን የመግደል እርምጃ የሳውዲ አረቢያ መንግስት ፖሊሲ አካል ሆኖ ከተፈፀመ፣  እነዚህ ግድያዎች ቀጣይነት ያለቸውና በሰብዓዊነት ላይ  የሚፈጸሙ ወንጀሎች ይሆናሉ።

የባለ 73 ገጽ ሪፖርት እንደሚለው “” ተኩስ በእኛ ላይ እንደ ዝናብ አወረዱብን’ ፣   በየመን እና ሳውዲ ድንበር ላይ በሳውዲ አረቢያ የተፈፀመ የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጅምላ ግድያ"”   የሳውዲ ድንበር ጠባቂዎች ብዙ ስደተኞችን ለመግደል ፈንጂ መሳሪያ እንደተጠቀሙ፣  ሌሎች ስደተኞችን በቅርብ ርቀት እንደተኮሱባቸውና ብዙ ሴቶችን እና ህጻናትን ጨምሮ፣ ሰፊ እና ስልታዊ በሆኑ ጥቃቶች መግደላቸውን አረጋግጧል። በአንዳንድ አጋጣሚዎች፣ የሳዑዲ ጠረፍ ጠባቂዎች ስደተኞቹን በየትኛው አካላቸው ላይ እንደሚተኩሱባቸው እየጠየቁ በቅርብ ርቀት ተኩሰው ገለዋቸዋል። በተጨማሪም፣ እነዚህ የሳውዲ ድንበር ጠባቂዎች ወደ የመን ለመመለስ የሞከሩ ስደተኞችንም ፈንጂ መሳሪያ ተኩሰውባቸዋል።

በሂዩማን ራይትስ ዎች ድርጅት የስደተኞችና ፍልሰተኞች መብቶች ተመራማሪ የሆኑት ናዲያ ሃርድማን እንደሚሉት "የሳዑዲ ባለሥልጣናት በነዚህ ሩቅ በሆኑ ድንበር አካባቢዎች ከቀረው ዓለም እይታ በተሰወረ መልኩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችና ጥገኝነት ፈላጊዎችን ይገድላሉ። “የሳውዲን ገፅታ ለመገንባት ለጎልፍ ፕሮፌሽናል፣ ለእግር ኳስ ክለብ እና ለዋና ዋና መዝናኛ ዝግጅቶች ግዥ በቢሊዮኖች የሚቆጠር ሀብት ወጪ ማድረጋቸው በእነዚህ ዘግናኝ ወንጀሎች ላይ ያለውን ትኩረት ማዛባት የለበትም"

ታህሳስ 4/2022 የተለቀቀ የቲክቶክ ቪዲዮ እንደሚያሳየው 47 ያህል የስደተኞች ቡድንን የሚያሳይ ሲሆን 37ቱ ሴቶች ናቸው፡፡ በሳውዲ አረቢያ ውስጥ ካለው ከአል-ታቢት የስደተኞች ካምፕ ለመሻገር ገደላማ ሥፍራ ላይ ሲሄዱ ያሳያል። © 2022 private

በሂዩማን ራይትስ ዎች ከመጋቢት 2022 እስከ ሰኔ 2023 ባለው ጊዜ ውስጥ የየመን-ሳዑዲን ድንበር ለመሻገር የሞከሩትን 38 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችና ጥገኝነት ፈላጊዎችን እና 4 ዘመድና ጓደኞቻቸውን ጨምሮ ለ42 ሰዎች ቃለ መጠይቅ አድርጓል። የሂዩማን ራይትስ ዎች ማህበራዊ ድረ-ገፆች ላይ የተለጠፉ፣ ከሌሎች ምንጮች የተገኙና በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ስኩዌር ኪሎሜትሮችን ካካለሉ የሳተላይት ምስሎች የተገኙ ከ350 በላይ ቪዲዮዎችን እና ፎቶግራፎችን መርምሯል።

ሂዩማን ራይትስ ዎች ለሳውዲ እና የሁቲ ባለስልጣናት ጽፏል። የሃውቲ ባለስልጣናት ኦገስት 19፣ 2023 ለደብዳቤያችን ምላሽ ሰጥተዋል።

በግምት 750,000 ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረቢያ ውስጥ እየሠሩ ይኖራሉ። ብዙ ኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች ቢኖሩአቸውም በቅርቡ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል እንደነበረው በጦር መሣሪያ የታገዘ አሰቃቂ ግጭት፣ አብዘኛዎቹ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ደግሞ በኢትዮጵያ ውስጥ በሚደርስባቸው የከፋ ሰብአዊ መብት ጥሰት ምክንያት አገራቸውን ጥለው ይሰደዳሉ።

ሂዩማን ራይትስ ዎች በየመንና ሳውድ ድንበር አካባቢ የተፈፀሙ የስደተኞችን ግድያ ከ2014 ጀምሮ በሰነድ ያዘጋጀ ሲሆን፣ ግድያዎቹም ሆን ተብለው የተፈፀሙና የሟቾችም  ቁጥር የበዛና የአገዳደላቸው ሁኔታም የከፋ ነው።

ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች በባህር ላይ ለመጓዝ ምቹ ባልሆኑ መርከቦች የኤደንን ባህረ–ሰላጤ እንዳቋረጡ ተናግረዋል። ከዚያም የየመን ህገወጥ ሰው አዘዋዋሪዎች በሳውዲ ድንበር በሁቲ ታጣቂ ቡድን ቁጥጥር ሥር ወደሚገኘው ሰዓዳ ግዛት ወስደዋቸዋል።

ብዙዎች የሁቲ ኃይሎች ከህገ–ወጥ አዘዋዋሪዎች ጋር እንደሚሠሩና እንደሚዘርፏቸው ወይም ስደተኞችን ወደ ማቆያ ማዕከላት እንደሚያስተላልፉ እና ሰዎች "የመውጫ ክፍያ" እስኪከፍሉ ድረስ በዚያ እንግልት ይደርስባቸዋል ብለዋል።

በሳአዳ ጠቅላይ ግዛት፣ ከየመን ወደ ሳዑዲ አረቢያ የሚያስገባ የስደት መንገድ አጠገብ በሳተላይት  ምስሎች  ተለይተው የሚታዩ የሳዑዲ ድንበር ጠባቂ ቦታዎች እና የጥበቃ መንገዶች 3D ሞዴል። አሰቃቂ © Human Rights Watch

እስከ 200 የሚደርሱ ስደተኞች በቡድን ሆነው ወደ ሳውዲ አረቢያ ድንበር ለመሻገር በየጊዜው ይሞክራሉ፣ ብዙ ጊዜ የሳዑዲ ድንበር ጠባቂዎች ወደ ኋላ ከገፏቸው በኋላ ብዙ ሙከራ ያደርጋሉ። ስደተኞች ቡድኖቻቸው ከወንዶች የበለጠ ሴቶች እንደሚበዙ ተናግረዋል ። ሂዩማን ራይትስ ዎች ከእነዚህ መረጃዎች ጋር የሚጣጣሙ የሳውዲ ድንበር ጥበቃ ቦታዎችን ከሳተላይት ምስሎች ለይቷል። በተጨማሪም ሂዩማን ራይትስ ዎች ከጥቅምት 11/2021 እስከ ጥር 1/2023 በአንዱ የሳውዲ የድንበር ጥበቃ ጣቢያ አካባቢ ከደፈጣ የተጠበቀና ፈንጂን መቋቋም የሚችል የሚመስል ተሽከርካሪ መታየቱን ለይቷል። ተሽከርካሪው በጣራው ላይ የተገጠመ ከባድ መትረየስ ያለው ይመስላል።

ከሳውዲ ድንበር ጠባቂዎች አቅጣጫ በሞርታር ፕሮጄክታይሎች እና በሌሎች ፈንጂ መሳሪያዎች ድንበሩን እንዳቋረጡ ጥቃት እንደደረሰባቸው በቡድን የሚጓዙት ሰዎች ገልጸዋል። የሳውዲ ድንበር ጠባቂዎች ፈንጂ መሳሪያዎችን ስለመጠቀማቸው ቃለ-መጠይቅ የተደረገላቸው ሰዎች 28 ክስተቶችን በመግለፅ አስረድተዋል። በሕይወት የተረፉ ሰዎችም ሳውዲዎች አንዳንድ ጊዜ በማቆያ ቦታዎች እንደሚያግቷቸውና፣ ለወራት እንደሚያቆዩአቸው ገልፀዋል።

ሁሉም አስፈሪ ትዕይንቶችን ነው የገለጹት ፡ የሴቶች፣ የወንዶች እና የህፃናት አካላት ክፉኛ ቆስለው በተራራማ መልክዓ ምድር ላይ ተበታትነዋል ፣ ቀድሞውንም የሞቱ እና የተቆራረጡ ናቸው። አንድ ሰው ሲናገር “መጀመሪያ አብሬአቸው የበላሁ የሚታወቁ ሰዎች የነበሩና በዚያ የሞቱ ነበር” ብሏል። “ሰውነታቸው በየቦታው ስለተወረወረ ማንነታቸውን ለማወቅ የማይቻል አንዳንድ ሰዎችም አሉ። አንዳንድ ሰዎች ደግሞ ለሁለት ተሰንጥቀዋል።

በሂዩማን ራይትስ ዎች ዲጂታል ምርመራ መሠረት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተለጠፉ ወይም በቀጥታ ወደ ሂዩማን ራይትስ ዎች የተላኩ ቪዲዮዎችና የተረጋገጡና በጂኦግራፊያዊ ጠቋሚዎች የተለዩ የሞቱ እና የቆሰሉ ስደተኞች በመንገድ ላይ፣ በካምፖች እና በህክምና ተቋማት አካባቢ ይታያሉ። የጂኦስፓሻል ትንታኔ በስደተኞች ካምፖች አቅራቢያ የቀብር ቦታዎች መጨመራቸውንና የድንበር ደህንነት መሠረተ ልማቶችም መስፋፋታቸውን አረጋግጧል።

በአልራቅዋ የስደተኞች ካምፕ አቅራቢያ በሚገኙ የሳተላይት ምስሎች ላይ የቀብር ቦታዎች የሚገኙበት ቦታ። ምስል: የካቲት 9,2022 © 2023 Maxar Technologies. ምንጭ፡ Google Earth

የአለም አቀፍ የስቃይ ሰለባዎች ማቋቋሚያ ምክር ቤት አባላት ገለልተኛ የፎረንሲክ ኤክስፐርት ቡድን፤ አለም አቀፍ የታዋቂ የፎረንሲክ ባለሙያዎች ቡድን የስደተኞችን መቁሰል፣ መጎዳትና መሞት መንስኤ የሚያሳዩ ቪዲዮዎችን እና ፎቶግራፎችን ተንትነው አረጋግጠዋል። አንዳንድ ጉዳቶች “ሙቀትን እና ሰውነትን ለመበታተን አቅም ካላቸው ጥይቶች ፍንዳታ ጋር መጣጣማቸውን፣” ሌሎች ደግሞ “ከጥይት ምት ቁስሎች ጋር የሚጣጣሙ ባህሪዎች” እና በአንድ አጋጣሚ “ቃጠሎዎች ይታያሉ” ሲሉ ደምድመዋል።

በትናንሽ ቡድን ወይም በየግላቸው የሚጓዙ ሰዎች አንዴ የየመን እና የሳዑዲ ድንበር ሲሻገሩ ጠመንጃ የያዙ የሳዑዲ ጠረፍ ጠባቂዎች ጥይት እንደተኮሱባቸው ተናግረዋል። እንዲሁም ስደተኞቹ ድንበር ጠባቂዎቹ በድንጋይና በብረት ዘንግ እንደደበደቡዋቸው ገልፀዋል። 14 ቃለ መጠይቅ የተደረገላቸው ሰዎች ከቅርብ ርቀት በመተኮስ ጥቃቶች እንደሚፈፀሙ መስክረዋል ወይም እነሱ ራሳቸው ቆስለዋል። ስድስቱ በፈንጂ መሳሪያዎች እና በተተኮሰ ጥይት ኢላማ ተደርገዋል።

አንዳንዶቹ እንደገለፁት የሳዑዲ ድንበር ጠባቂዎች ከድንበር ጥበቃ ጣቢያቸው ወርደው የተረፉትን ይደበድባሉ። የድንበር ጠባቂዎች በህይወት የተረፉት እንዲደፈሩ እንደሚያደርጉ፣ ለመድፈር ፈቃደኛ ያልሆነውን ስደተኛ ከገደሉ በኋላ አንድ የ17 አመት ልጅ የድንበር ጠባቂዎች እሱን እና ሌሎች በህይወት የተረፉትን ሁለት ሴት ልጆች እንዲደፈሩ ማስገደዳቸውን ተናግሯል።

ሳውዲ አረቢያ በስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ላይ በፈንጂና በቅርብ ርቀት በመተኮስ ማጥቃትን ጨምሮ ገዳይ ሃይልን ለመጠቀም የተቀመጠ ማንኛውንም ፖሊሲ በአስቸኳይ መሻር አለባት። መንግስት በየመን ድንበር ላይ ህገወጥ ግድያ፣ ማቁሰል እና ሰቆቃ የሚፈፅሙትን የደህንነት አባላትን መርምሮ በተገቢው መቅጣት ወይም መክሰስ ይገባል።

ጉዳዩ የሚመለከታቸው መንግስታት ሳውዲ አረቢያ የዚህን አይነት ገዳይ ፖሊሲ እንድታቆምና ተጠያቂነት እንዲሰፍን ግፊት ማድረግ አለባቸው። ከዚህ ጋር በተገናኘ የሚመለከታቸው መንግስታት በድንበር ላይ እየተፈጸሙ ያሉ ጥሰቶች ላይ ታማኝ በሆነ መልኩ በሳዑዲ እና የሁቲ ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ መጣል አለባቸው።

በተባበሩት መንግስታት (UN) የሚደገፍ ምርመራ በማቋቋም በስደተኞች ላይ የሚደርሰው በደል፡ ግድያዎችም በሰብአዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች ስለመሆናቸው መመርመር አለበት።

ሃርድማን "የሳውዲ ድንበር ጠባቂዎች ባልታጠቁ ሰላማዊ ዜጎች ላይ እንደሚተኩሱ ያውቃሉ ወይም ማወቅ ነበረባቸው" ብላለች። "በኢትዮጵያውያን ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ላይ ለሚፈፀሙ ወንጀሎች ፍትህ ካልተገኘ ተጨማሪ ግድያዎችንና እንግልቶችን ያባብሳል።"

Your tax deductible gift can help stop human rights violations and save lives around the world.