Skip to main content

ባስቸኳይ ይፋ Eንዲወጣ

ሶማሊያ፦ የጦርነት ወቅት ወንጀል በሞቃዲሾ የተባበሩት መንግስታት በህዝብ ደህንነት ጥበቃ ላይ ማትኮር Aለበት።

(ናይሮቢ፦ Oገስት 13፣ 3007) የIትዮጵያና የሶማሊያ ወታደሮች፤ Eንዲሁም ልዩ
ልዩ የAመፀኛ ሃይሎች በAሁኑ ጊዜ ሞቃዲሾ ውስጥ የጦርነት ወቅት ሕግጋትን
በመጣስ በህዝብ ላይ ከፍተኛ በደልና ስቃይ ማስከተላቸውን የሰብAዊ መብቶች
ታዛቢ (ሂዩማን ራይትስ ዋች) በዛሬው Eለት ይፋ ባወጣው ሪፖርት Aስታውቋል።
በተጨማሪም የተባበሩት መንግስታት የሴኪዩሪቲ ካውንስል የሶማሊያን ሁኔታ
ገምግሞ የሰላም ጥበቃ ኃይል ለመላክ ሲወስን የህዝብ ደህንነት ዋስትናንም ትኩረት
Eንዲሰጠው የሰብAዊ መብቶች ታዛቢ Aጥብቆ Aሳስቧል።
በ113 ገጾች የተጠናቀረው “የሞቃዲሾ ህዝብ ጥቃት” የተሰኘው ሪፖርት ለመጀመሪያ
ጊዜ በስፍራው የተካሄደ ምርመራ ሲሆን፤ ባለፉት ማርች Eና ኤፕሪል 2007
በሞቃዲሾ ተካሂዶ የነበረ ውጊያ ስላደረሰው ከፍተኛ ጥፋትና በመቶ ለሚቆጠሩ
ሰዎች Eልቂትና ለAራት መቶ ሺህ ሰዎች ስደት ምክንያት መሆኑን ይዘግባል።
የሰብAዊ መብቶች ታዛቢ ዋና ዳይሬክተር ኬን ሮዝ Eንዳሉት “በውጊያው
የተሳተፉት የተለያዩ ኃይሎች በከተማው ለሚኖረው ህዝብ የነበራቸው ግዴለሽነት
ወንጀለኛ ያደርጋቸዋል። ይብሱን ደግሞ የተባበሩት መንግስታት ሴኪዩሪቲ
ካውንስል ለዚህ ወንጀል ያሳየው ደንታቢስነት በደሉን የከፋ ያደርገዋል።”
የሰብAዊ መብቶች ታዛቢ ባካሄደው ምርመራ፤ በጊዜው የተፈጸሙ በርካታ የጦርነት
ወቅት ወንጀሎችን ዘግቧል። ለምሳሌ በሶማሊያ ሽፍቶች ከተፈጸሙት ሕገወጥ
ተግባራት መካከል የሚከተሉት ይገኙባቸዋል፦ በርካታ ነዋሪዎች ካሉበት መንደር
ሞርታር መተኮስና ታጣቂዎችን ማሰማራት፣ የሶማሊያ የሽግግር መንግስት Aባላትን
Aድኖ መግደል፣ የጦር ምርኮኞችን ሰብስቦ መፍጀትና Aካላቸውን መቆራረጥ።
የሶማሊያን የሽግግር መንግስት የሚደግፈው የIትዮጵያ ጦር Aባላትም Eንዳሻቸው
ሞቃዲሾ ውስጥ የህዝብ መኖሪያ Aካባቢዎችን በሮኬት፣ በሞርታርና መድፍ
በመደብደብ፤ ወታዶሮቹም ሆስፒታሎችን በመውረርና የህክምና ቁሳቁስን
በመዝረፍ፤ Aንዳንዴም ይሁን ብለው ግለሰቦችን በመግደል የጦርነት ወቅት
ሕግጋትን መጣሳቸውን የሰብAዊ መብቶች ታዛቢ Aረጋግጧል።
የሶማሊያ የሽግግር መንግስት ኃይሎች ከIትዮጵያ ጦር ዝቅተኛ ቦታ
ቢኖራቸውም፤ ውጊያ በሚካሄድባቸው Aካባቢዎች ለሚገኙ ኗሪዎች በቅድሚያ
ማስጠንቀቂያ ባለመስጠት፣ የህዝብን ንብረት በመዝረፍ፣ ለተሰደዱ የከተማው ሰዎች
ለሚደረጉ Eርዳታዎች Eንቅፋት በመፍጠርና በEስራት ላይ የሚገኙ ዜጎችን
በማጎሳቆል ወንጀል ፈጽመዋል።
“ሽፍቶች ከህዝብ መሃል ተሰማርተው Eንደነበር ግልፅ ቢሆንም፤ በዚህ ሳቢያ
የIትዮጵያ ጦር የነዋሪዎችን መንደር በሮኬትና በቦምብ መደብደብ Aይገባውም
ነበር።” ሲሉ የሰብAዊ መብቶች ታዛቢ ዳይሬክተር ተናግረዋል።
ይህ የሰብAዊ መብቶች ታዛቢ ዘገባ ይፋ የወጣበት የዛሬው ቀን፤ የተባበሩት
መንግስታት የሴኪዩሪቲ ካውንስል የሶማሊያን ጉዳይ ለመመልከት ጉባዔ
የሚከፍትበት Eለት ነው። የሴኪዩሪቲ ካውንስሉ በጉባዔው ወደ ሶማሊያ ስለሚላከው
ባለ1500 Aባላት የAፍሪካ Aንድነት ድርጅት ተልEኮ Eንደሚነጋገርና፤ ይህንንም
ተልEኮ የተባበሩት መንግስታት ኃይል ለማድረግ Eንደሚወያይ ይታወቃል።
የሶማሊያ የሽግግር ፌዴራላዊ መንግስት በIትዮጵያ ተደግፎ በሞቃዲሾ በጃንዋሪ
2007 ስልጣን ከጨበጠ ወዲህ ከከተማው ውስጥ ውጊያ Eየተባባሰ መጥቷል።
በዲሴምበር 2006 የIትዮጵያ ጦር በዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍ የEስላማዊ
ፍርድቤቶችን ቅንጅት Aመራር ከሞቃዲሾና ከማEከላዊ ደቡብ ሶማሊያ ፈንቅሎ
Aስወጥቷል።
ከጃንዋሪ 2007 ጀምሮ የEስላማዊ ፍርድቤቶች ታጣቂ ሚሊሻዎችና የተባበሩ የAመፅ
ወገኖች በAጥፍቶ የመጥፋት ጥቃትና የሽግግሩን መንግስት ሲቪል Aባሎች
በመግደል ሽብር በማካሄድ ላይ ናቸው። በተጨማሪም ሽፍቶቹ ከሞቃዲሾ ህዝብ
መሃል ተደብቀው ሞርታር በመተኮስና የህዝቡን ደህንነት ከAደጋ ላይ በመጣል
የጦርነት ወቅት ሕግጋትን Aፍርሰዋል።
በማርች 29 ቀን የIትዮጵያ ኃይሎች ሁለት Aቢይ የፀረ-ሽፍታ ዘመቻዎችን
በሞቃዲሾ Aካሂደው ነበር። በEነዚህ ዘመቻዎች ለሰላማዊ ህዝብ ግዴለሽነት
በተሞላበት ሁኔታ ሽፍቶች የሚገኙባቸውን መንደሮች በሞርታር፣ በካቱሻ ሮኬቶችና
በመድፍ ደብድበዋል።
ከኤፕሪል18 Eስከ 26 በተካሄደው ሁለተኛ ዘመቻ የIትዮጵያ ወታደሮች ሌሎች
የከተማውን Aካባቢዎች Iላማ በማድረግ ከፍተኛ ጥፋትና በመቶ የሚቆጠሩ
ሰዎችን Eልቂት Aስከትለዋል። በሁለቱ ውጊያዎች ምን ያህል የከተማው ኗሪዎች
ህይወታቸውን Eንዳጡ በትክክል ባይታወቅም 1300 ያህል ሰዎች መገደላቸው
ይገመታል።
የIትዮጵያ መንግስት በሶማሊያ ጉዳይ ለመግባቱ ምክንያት የAካባቢው ፀጥታ
መደፍረስ ለኤርትራ የEጅ Aዙር ጥቃት የሚፈጥረው የተመቸ ሁኔታ፣ Eንዲሁም
ሁለት የIትዮጵያ የAመፅ Eንቅስቃሴዎች ሶማሊያ ውስጥ መግባታቸው ነው።
በጃንዋሪ 2007 የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት በደቡብ ሶማሊያና ኋላም በሰሜን
ምስራቅ ፑንትላነድ ተደጋጋሚ የAየር ጥቃት Aካሂዷል። Eነዚህ ጥቃቶች የAሜሪካ
ጦር ከሶማሊያ በ1994 ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የመጀመሪያዎቹ ናቸው። የሶማሊያ
የEስላማዊ ፍርድቤቶች ለAንዳንድ ከAለም Aቀፍ የሽብር Aውታር ጋር ግንኙነት
ላላቸው ግለሰቦች፤ ለምሳሌ በ1988 ኬንያና ታንዛኒያ ውስጥ የዩናይትድ ስቴትስ
ኤምባሲን በቦምብ ላጠቁት ሰዎች መጠለያ ሆኗል ሲል የAሜሪካ መንግስት
ወንጅሏል።
“ዋነኛው የመጀመሪያው ውጊያ በኤፕሪል ካለቀ በኋላ የIትዮጵያና የሶማሊያ
መንግስት ወታደሮች በየቦታው የህዝቡን መብት Eየረገጡ ይገኛሉ” ብለዋል
የሰብAዊ መብቶች ታዛቢ ዳይሬክተር ኬን ሮዝ። “ዘላቂ የፀረ-ሽብር መፍትሄ
የሚገኘው ሰብAዊ መብቶች ሲከበሩና ወንጀል ለፍርድ ሲቀርብ ብቻ ነው።”
የIትዮጵያና የሶማሊያ መንግስታት የሚያካሂዱትን የማን Aለብኝ ሕገ-ወጥነት
ይገቱ ዘንድ የተባበሩት መንግስታትን ሴኪዩሪቲ ካውንስልና ሌሎች Aበይት የAለም
Aቀፍ ድርጅቶችን Eንዲያስገድዷቸው የሰብAዊ መብቶች ታዛቢ Aሳስቧል።
ሁኔታው ያሳሰባቸው Aገሮችም የተባበሩት መንግስታት የሰብAዊ መብቶች
ተቆጣጣሪና ዘጋቢ ተልEኮ Eንዲፈጥርና ወደ ሶማሊያ Eንዲልክ መጠየቅ፤
Eንዲሁም Aስፈላጊውን ድጋፍ መስጠት Aለባቸው።
“የሞቃዲሾ ህዝብ ጥቃት” በሚል ርEስ የቀረበውን የሰብAዊ መብቶች ታዛቢ ዘገባ
ለመመልከት የሚከተለውን ይጎብኙ፦
https://www.hrw.org/reports/2007/somalia0807/
የሰብAዊ መብቶች ታዛቢ በዘገባው ላይ ያቀረበውን Aስተያየት ለማዳመጥ
የሚከተለውን ይጎብኙ፦
https://www.hrw.org/audio/2007/english/somalia08/somali16599.htm

Your tax deductible gift can help stop human rights violations and save lives around the world.

Related content