ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2017 የተወሰነ መሻሻሎችን ያሳየች ቢሆንም የሚፈለገዉን መሰረታዊ የሰብዐዊ መብቶች ማሻሸያ እምብዛም አላደረገችም። ይልቁንም መሰረታዊ የሰዎች መብትና ነጻነትን አፍና ለመቀጠል በጣም የተራዘመዉን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ የጸጥታ ሀይሎችን ጥቃት እንዲሁም አፋኝ ህጎችን በማውጣት ተጠቅማበተለች።
በጥቅምት ወር 2016 የታወጀውና ለ10 ወራት የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ በርካቶችን ለስራት ዳርጓል። አዋጁን ተከትሎ የጅምላ አስራት፣ በየእስር ቤቱ መደብደብ እንዲሁም የመሰብሰብ፣ ሀሳብን በናጻነት የመግለጽ እና የመደራጀት መብት ላይ እቀባ ተጥሎ ቆይቷል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መጠነ ሰፊ እና አፋኝ ቢሆንም የተፈጠረው ዐንጻራዊ መረጋገት ሰለማዊ ሰልፈኞቹ አንግቦ የተነሱትን ጥያቀዎች ለመፍታት ለመንግስት ምቹ አገጣሚ ነበር።
ይሁን እንጂ መንግስትይህን ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም ሰልፈኞቹ ስያነሱ የነበሩትን የፖለቲካ ምህዳር መጥበብ፣ የጸጥታ ሀይሎች ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ እና በሀይል ከመሬታቸው መፈናቀልን የመሳሰሉትን የሰብዐዊ መብት ጥያቀዎች አልመለሰም። ይልቁኑ የመንግስት ባላስልጣናት የጸረ-ሙስና ማሻሸያን የካብኔ ሹም-ሺረትን፣ ከእስር የተረፉት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር መወያየት እንደሚፈልጉ እንዲሁም ለወጣቶች የስራ እድል ለመክፈት እና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን በቁርጠንኝት እንደሚሰሩ አስታወቁ።
በሀገሪቱ አሁንም የፖለቲካ ምህዳሩ እንደ ጠበ ነው። የገዥው ፓርቲ ጥምረት የፌዴራል አና የክልል ምክር ቤቶችመቀመጫዎች 100% ጠቅልሎ ተቆጣጥሮታል። የሰቪክ ማህበራት እና ነጻ የሚዲያ ተቋማት ላይ የተጣለው መጠነ-ሰፊ ክልከላ፣ እውነተኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ማዳከም፣ መንግስትን የሚደግፉ ግለሰቦች ላይ የሚደርሰው ወከባ እና ህገ-ወጥ እስራት የተቃዉሞ ድምጾች የሚተነፍሱበትን የፖለቲካ ምህዳር በእጅጉ ወስኖታል።
የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን ለመመርመር መንግስት በተደጋገሚ ቃል የገባ ቢሆንም እስከ አሁን ታማኝ እና ገለልተኛ ምርመራ አለማድረጉ የአለም ዓቀፍ የምርመራ ቡድን አሁንም አስፈላጊ መሆኑን አመላካች ማስረጃ ነው። ገለልተኛ ያልሆነው የኢትዮጵያ ሰብዐዊ መብቶች ኮሚሽን የሚያደርገው ምርመራ በተደጋገሚ ተዐማኒነት ማግኘት አልቻለም።
ስለ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ
2017 በመላው ሀገሪቱ ጥቅምት 2016 መጀመሪያ የተቀጣጠለውን ህዝባዊ እምቢተኝነት ተከትሎ በታወጀውና በኋላም በመጋቢት ወር ዉስጥ ለተጨማሪ 4 ወራት ተራዝሞ ነሀሴ 4 ቀን በተነሳው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ሥር ነበር ያሳለፈችው። የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ በወሰዱት እርምጃ ከ1000 በላይ ዜጎች ሲገደሉ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩት ደግሞ እስር ቤት ታጉረዋል።
የአስቸካይ ጊዜ አዋጁን ለመተግበር የወጣው ህግ በጣም አፋኝ እና መጠ-ነሰፊ የነጻ ሀሳብ፣ የመደራጀት እና ሰለማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቶችን በመላ ሀገሪቱ አግዶ ነበር። ይህ እርምጃ መንግስት ችግሩን በወታደራዊ ሀይል ለመፍታት የስቀመጠዉን አቅጣጫ በግልጽ ያመላከተ ነው። በዚህ ህግ መንግስት እውቅና ያልሰጠዉን ሁሉም ሰላማዊ ሰልፎችን አግዶ ነበር። በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት በተወሰኑ አከባቢዎች ከፍርድ ቤት ትእዛዝ ዉጭ ዜጎችን በጅምላ ማሰርን የፈቀደ ነበር። የጉልበት ስራን ጭምር የሚያካትት የታሃድሶ እስራትንም ፈቅዶ ነበር።
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወቅት ወታደሮች በብዛት ወደ ኦሮሚያ እና አማራ ክልል ተሰማርተዋል። የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች መንግስት ባቀረበው ቁጥር መሰረት እንኳ ፪፲፻ ሰዎችን በታሃድሶ ካምፕ ዉስጥ በጅምላ አስሯል። እስረኞች በእስር ቤት ዉስጥ መደብደባቸዉን እና የመንግስትን ፖሊሲ በግድ እንዲቀበሉ መደረጋቸው ተናግሯል። እስረኞቹ የታሰሩባቸው ቦታዎች ነባር እስር ቤቶች፣ ወታደራዊ ካምፖች እና በግዜያዊ ኮንቴይነሮች ዉስጥ ነበር። አንዳንዶች በእስር ቤት ዉስጥ ሰቆቃ እንደተፈጸመባቸው ገልጸዋል። አርቲስቶች፣ የፖለቲካ መሪዎች እና ጋዜጠኞች ፖለቲካዊ ክስ ተመስርቶባቸዋል።
በህግ ተመዝግቦ በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሰው ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ፡ የኦሮሞ ፌዴራልስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ህገ መንግስቱን ጥሰሃል በሚል ክስ ተወንጅለው ከመጋቢት ወር ጀምሮ እስር ላይ ይገኛሉ። ዶር መረራም እንዲሁ ፖለቲካዊ ክስ ተመስርቶባቸው በእስር ላይ ያሉትን ሌሎች የኦፌኮ መሪዎችን የፓርቲዉ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑትን እነ አቶ በቀላ ገርባን ተቀላቅሏል። ይህ ሪፖርት ሲዘጋጅ ወቅት በአስቾካይ ግዜ አዋጁ ወቅት ተይዞ ከነበሩት በመንግስት መረጃ መሰረት 8000 ሰዎች አሁንም እስር ቤት ናቸው።
ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ እና የመሰባሰብ ነጻነት
መንግስት ሚዲያዉን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮታል። ይህ ሁኔታ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወቅት በጣም አይሎ ስለነበር ዜጎች ከመንግስት አመለካከት ነጻ የሆነ መረጃን ለማግነት በእጅጉ ተቸግረው ነበር። ብዙ ጋዜጠኞች እራሳቸዉን ሳንሱር ማድረግ፣ ወይንም ወከባ እና እስራት ወይንም መሰደድ ግድ ሆኖባቸዋል። ከ2010 ጀምሮ ቢያንስ 85 ጋዜጠኞች ከኢትዮጵያ ተሰደዋል። ከእነዚህም ወደ 7 የሚሆኑት ጋዜጠኞች የተሰደዱት በ2017 ነው።
እስክንድር ነጋ እና ዉብሸት ታዬን ጨምሮ ብዙ ጋዜጠኞች በጸረ ሽብር ህጉ ተወንጅለው እስካሁን ድረስ በእስር ቤት እንዲቆዩ ተደርገዋል።
ይህ መንግስት ጋዜጠኞችን ከማስፈራረት በተጨማሪ ፣ የማስታወቂያ፣ የማተሚያ እና የማሰራጫ ተቋማትን ማወካብ ነጻ ሚዲያን የሚያዳክምበታንዱና ዋነኛው ዘዴ ነው።
ጥሩ እና ገለልተኛ የሀገር ዉስጥ ሚዲያ በመጥፋቱ የተነሳ፣ መህበራዊ ሚዲያ እና ከዉጪ ሀገር የሚተላለፉ የዲያስፖራ ቴሌቭዥን ጣቢያዎች መረጃን በማደረስ ላይ ከፍተኛ ሚና ተጫውተው ነበር። መንግስት በበኩሉ መህበራዊ ሚዲያን እና የዲያስፖራ ቴሌቪዥኖችን ተደራሽነት ለመከላከል ከፍተኛ ጥረት አድርጎ ነበር። በአስቸካይ ጊዜ አዋጁ ወቅት የዲያስፓራ ቴሌቪዥኖችን ማየት ከልክሏል፣ ወደ ሀገሪቱ የሚተላለፉትን የዉጪ ራዲዮ እና ቲቪዮችን አግዷል። በዲያስፖራ ጣቢያዎች ዉስጥ የሚሰሩ ጋዜጠኞችን ቤተሰብ እና የዜና ምንጫቸዉን ኢላማ አድርገዋል። ሚያዝያ 2017 ሁለቱ የዲያስፖራ ተለቪዥን ጣቢያዎች ማለትም ኦ.ኤም.ኤን እና ኢሳት በጸረ ሽብር ህጉ ተከሰዋል። የኦኤምኤን ሥራስኪያጅ አቶ ጀዋር መሃመድ ሚያዚያ 2017 በወንጀል ህግ ተከሰዋል።
መንግስት ላይ ትችት የሚያንጸባርቁ ድረ-ገጾችን እና የማህበራዊ ሚዲያ መተግበሪያዎችን መንግስት በተደጋገሚ አግዷል። የተቃውሞው ትኩሳት በሚያልባቸው ግዜያትየሀገር አቀፍ ፈተና በሚሰጥበት ወቅት፣ ፈተና ሾልኮ ይወጣል በሚል ፍራቻ መንግስት የኢንተርኔት አገልግሎትን ሙሉ በሙሉ አጥፍቷል።
የ2009 ዓ.ም የለጋሾች እና ሲቪክ ማህበራት አዋጅ (CSO law) መንግስታዊ ያልሆኑ ገለልተኛ ተቋማትን አቅም በእጅጉ አዳክሞታል። ህጉ ከ10 % በላይ የበጀት ድጎማን ከዉጪ የሚያገኙ ተቋማት የሰብዐዊ መብት ስራዎችን፣ የግጭት አፈታት እና የህጻናት፣ የሴቶች እንድሁም የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ ላይ እንዳይሰሩ ይከለክላል።
በእስር ቤት ዉስጥ የሚፈጸም ሰቆቃ እና የጅምላ እስራት
የጅምላ እስራት እና እስር ቤት ዉስጥ የሚፈጸመው ሰቆቃ ኢትዮጵያ ዉስጥ አሁንም እንኳ ትልቅ ችግር ነው። የኢትዮጵያ የጸጥታ ሀይሎች፣ ሲቪል ለበስ የደህንነት ሀይሎች፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ ልዩ ፖሊስ እና መከላከያ ሀይሎች በመደበኛ እና ድብቅ እስር ቤቶች ዉስጥ መረጃን በጉልበት ለመቀበል ሲባል የፖለቲካ እስረኞች ላይ ከባድ ግፍ ፈጽመዋል፣አንገላተዋል።
በ2015/2016 እ.ኤ.አ ተቃዉሞ ሰልፍ እና በ2017 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት ተይዘው ከታሰሩት ብዙዎቹ በእስር ቤት እና በወታደራዊ ከምፖች ዉስጥ ግፍ እንደተፈጸመባቸው ይናገራሉ። ብዙ ሴቶች ጥበቃ ስር ባሉበት ወቅት በጸጥታ ሀይሎች መደፈራቸውን እና ጾታዊ ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ተናግረዋል። ይህን ወንጀል የፈጸሙ የጸጥታ ሀይሎች መመርመራቸዉን እና መቀጣታቸውን የሚያሳይ ምንም የሚታይ ምልክት የለም። የጸጥታ ሀይል ዉስጥ የነበሩ ግለሰቦች በእስር ቤት ዉስጥ ከእስረኞች መረጃን በሀይል ለመቀበል ሲባል በደል መፈጸማቸዉን ገልጸዋል።
በፖለቲካ ጉዳዮች ላይ የፍርድ ቤት አና የፍርድ ሂደት ገለልታኛነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል። ከአዲስ አበባ ዉጪ ባሉ እስር ቤት ዉስጥ የታሰሩ ግለሰቦች ክስ አይቀርብባቸዉም ወይንም ፍርድ ቤት አይቀርቡም።
የተቃዉሞ ድምጽን በሰላማዊ መንገድ የሚያሰሙ ግለሰቦች ብዙ ጊዜ በአፋኙ ጸረ ሽብር ህግ ይከሰሳሉ፣ አሸባሪ ተብለው ከተፈረጁት ሶስቱ ድርጅቶች ዉስጥ የአንዱ አባል ናቸው ተብሎ ይወነጀላሉ። ክሶቹ እስከ እድሜ ልክ እስራት የሚያስቀጡ ናቸው። ክስ ማቋረጥ ብዙም አልተለመደም። እስረኞች በህግ ከለላ ስር ስለሚፈጸምባቸው ጥቃት ለፍርድ ቤት ስናገሩ ዳኞቹ በቸልተኝነት ያልፋሉ። በመቶዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦች፣ የፖሊቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ ሰላማዊ ሰልፈኞች፣ ጋዜጠኞች እና አርቲስቶች በጸረ ሽብር ህግ ተወንጅለው እስር ቤት ይገኛሉ።
እነዚህን ውንጀላዎች ለማጣራት እንዲያስችል መንግስት በተባበሩት መንግስታት ድርጂት የጅምላ እስራት ጉዳዮች ዙሪያ የሚሰሩ የአለማቀፍ ቡድን ክስ ለመመርመር በ2005፣ በ2007፣ በ2009፣ በ2011 እና በ2015 ጥያቄ ብያቀርብም የኢትዮጵያ መንግስት ወደ ሀገሪቱ ገብቶ እንዳይሰሩ ፈቃድ ከልክሏል።
የሶማሌ ክልል የጸጥታ ሀይል ስለሚፈጽመው የመብት ጥሰት
በየጊዜው በዜጎች ላይ የሰብዐዊ መብቶች ጥሰት በመፈጸም የሚታወቀው የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ አባሎች ከባድ የሰብዐዊ መብት ረገጣዎችን መፈጸማቸውን እንደቀጠሉበት ነው። በሶማሌ ክልል ድንበር ላይ የሚኖሩ የኦሮሞ ማህበረሰቦች የታጠቁ የሶማሌ ልዩ ፖሊስ አባላት በቤቶቻቸው ላይ ተደጋገሚ ጥቃት መሰንዘራቸዉን ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ ግድያን፣ ዝርፍያን፣ ጥቃትን እና ከመሬት መፈናቀል እንዳስከተሉባቸው ገልጸዋል። ብዙ የሶማሌ ማህበረሰቦችም ባልተወቁ የኦሮሞ ግለሰቦች የበቀል እርምጃ እንደተወሰደባቸው ይናገራሉ። ህዩማን ራይትስ ዎች ይሄን ጥቃት ለማስቆም የፌዴራል መንግስት የወሰደው እርምጃ ስለ መኖሩ ምን መረጃ አልደረሰውም። በዚህ የድንበር ላይ ግጭት የተነሳ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ህዝብ ከቄየው ተፈናቅሏል።
የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ እ.ኤ.አ. በ 2008 የተቋመ ሲሆን ግልጽ የሆነ ሀላፊነት ሳይኖራቸው ነገር ግን በተግባር ለሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት ለዐብዲ ሞሃመድ ኦሜር (ሪፖርት) እንድያደርጉ ሆኖ ተቋቁመዋል። ይሄ ሀይል ያለ አንዳች ፍርድ ግድያን፣ አስገድዶ መድፈርን እና ከፍተኛ በደል በመፈጸም እንዲሁም የኦጋዴን ነጻ አዉጪን ይረዳሉ ተብለው የሚጠረጠሩ ግለሰቦችን በሶማሌ ክልል ዉስጥ በማሰቃየት ስማቸው ሲነሳ ይሰማል።
የክልሉ ፕሬዚዳንት አብዲ ኢሌይ የተቃዉሞ ድምጾችን የማፈን ፊላጎቱ በኢትዮጵያ ብቻ የተወሰነ አይደለም። በዉጭ ሀገራት የሚኖሩ የሶማሌ ክልል ተወላጆች ሰለማዊ ሰልፍ ሲወጡ ወይንም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ትችት በሚያቀርቡበት ጊዜ ቤተሰባቸውን በማፈላለግ መደብደብ፣ ማሰር እና ሀብት ንብረታቸዉን በመዝረፍ ዝም ያሰኛቸዋል።
ወሳኝ አለማቀፍ ባለድርሻዎች
በየጊዜው እያሽቆለቆለ ያለ የሰብዐዊ መብት አያያዝ ቢኖራትም ኢትዮጵያ ከለጋሽ ሀገራት እና ከጎረቤት ሀገራት ጠንካራ ድጋፎችን መግኘቷን ቀጥላለች። ምክንያቱም የአፍሪካ ህገራት አስተናጋጅ እና ስትራተጂካዊ አጋር በመሆኗ፣ ለመንግስታቱ ድርጅት ሰላም አስከባሪ ሀይል እና የአከባቢው ጸረ ሽብር እንቅስቃሴ ዉስጥ ባላት ተሳትፎ፣ በስደተኞች ጉዳይ ላይ ከምእራብ ሀገራት ጋር ባለት አጋርነት እንዲሁም አስመዝግባለች በሚባለው ኢኮኖሚያዊ እድገት የተነሳ ነው። ኢትዮጵያ የስደተኞች መነሻ፣ መተላለፊያ እና ለብዙ ስደተኞች ደግሞ መጠጊያም ነች።
የአዉሮፓ ፓርላማ እና የአሜሪካ ሴኔት እና የህዝብ ተዋካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ሰብዐዊ መብት አያያዝን ኮንነዉታል። የአዉሮፓ ፓርላማም ከ2015 የተቃዉሞ ሰልፍ ጀምሮ የተደረጉት ግድያዎች ላይ የመንግስታቱ ድርጅት የሚመረው ቡድን ምርመራ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቦ ነበር። ሚያዝያ 2017 የአዉሮፓ ህብራት ልዩ የሰብዐዊ መብቶች ተወካይ ኢስታቭሮስ ላምብሪዲኒስ ኢትዮጵያን በመጎብኘት ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለው የመብት ጥሰት አሳሰቢነት አስምረውበታል። አለም ባንክን የመሳሰሉ ሌሎች ለጋሾች የሰብዐዊ መብት አያያዙ ምንም ሳያሳስባቸው መደበኛ ስራቸውን ቀጥለዉበታል።
ኢትዮጵያ የመንግስታቱ ድርጅት የጸጥታ እና ሰብዐዊ መብቶች ምክርቤት አባል ብትሆንም ከመንግስታቱ ድርጅት ልዩ የምርመራ ቡድን ጋር ያላመተባበር ታሪክ ያለት ሀገር ነች። በ2006 በኤርትራ ጉዳይ ላይ የሚሰራ ራፖር ኢትዮጵያ ከገባ ወዲህ አንድም የመንግስታቱ ድርጅት ልዩ የምርመራ ቡድን ኢትዮጵያ ገብቶ እንዳይሰራ ከልክላለች። በእስር ቤት የሚፈጸም ሰቆቃን፣ ሀሳብን በነሳነት የመግለጽ እና ሰላማዊ ሰልፍ የመዉጣት መብትን የሚከታተሉ ራፖሮች ሀገሪቷን ለመጎብኘት ተደጋገሚ ጥያቄ ቢያቀርቡም እስከሁን አልተፈቀደላቸዉም።