ኢትዮጵያ፡- በጥቅምት ወር የብዙዎችን ህይወት ከቀጠፈው ግጭት ጋር በተያያዘ ፍትህ ሊሰጥ ይገባል

በጥቅምት ወር 2012 ዓ.ም. የብዙዎችን ህይወት በቀጠፈው ግጭት ላይ ምርመራ ከማካሄድ እና ለወደፊቱ ተመሳሳይ ጥቃቶች በጸጥታ ሀይሎች እንዳይፈጸሙ እና በማህበረሰቦች መካከል ተመሳሳይ ግጭቶች እንዳይከሰቱ ለመከላከል የሚያስችሉ እርምጃዎችን ከመውሰድ አንጻር የኢትዮጵያ መንግስት የወሰዳቸው እርምጃዎች አጥጋቢ ያለመሆናቸውን ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ድርጅት በዛሬው ዕለት ገለጸ። ግጭቱ ከተፈጠረ ስድስት ወራት ያለፉ ቢሆንም በኦሮሚያ ክልል ሁለት ከተሞች ውስጥ የሚኖሩት የግጭቱ ተጎጂዎች እና ቤተሰቦቻቸው በጸጥታ ሀይሎች እና በነውጠኞች ለተፈጸመባቸው ጥቃት አሁንም ፍትህ አላገኙም።

News